ጸሎት ቀዳሚ ሥራ
Sermon • Submitted • Presented
0 ratings
· 12 viewsNotes
Transcript
ጸሎት ቀዳሚው ሥራ
ከሁሉ በፊት
የሐዋሪያው ምክር ለቤተክርስቲያን
ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ፡፡
አማኞች ጌታን ለማምለክም ሆነ ለማገልገል በአንድነት ሲሰባሰቡ ቀዳሚ ተግባራቸው ጸሎት ሊሆን ይገባል፡፡«ወደ ተቀደሰ ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፥ በጸሎቴም ቤት ደስ አሰኛቸዋለሁ፤ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባላልና የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና ሌላ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያዬ ላይ እቀበላለሁ። » ይላልና በነቢዩ ኢሳ 56-7 እንግዲህ መታወቅ ያለበት ጸሎታችን የእግዚአብሔርን ፍቅርና ምህረት የወንጌል ሥጦታው ያህል ሊሰፋ የተገባው መሆኑ ነው፥፥
ኢሳ 56:7
ስለዚህ አማኞች ጌታን ለማምለክም ሆነ ለማገልገል በአንድነት ሲሰባሰቡ ቀዳሚ ተግባራቸው ጸሎት ሊሆን ይገባል፡፡«ቤቴ ለሕዝብ ሁሉ………… »ኢሳ56-7 እንግዲህ መታወቅ ያለበት ጸሎታችን የእግዚአብሔርን ፍቅርና ምህረት የወንጊል ሥጦታው ያህል ሊሰፋ ይገባል
I. ልመናና ጸሎት የቤተክርስቲያን ቀዳሚ ሥራ ጸሎት ማድረግ ሲሆን ጌታ ራሱ በወንጌላት ቤቴ ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባለል ነበር ያለው፡፡ ቤቱ የጸሎት ቤት እንጂ የሌላ አይደለም፡፡ የሰራናቸው አዳራሾች የጸሎት ቤት ካልሆኑ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ለመገመት ያስቸግራል፡፡
I. ልመናና ጸሎት የቤተክርስቲያን ቀዳሚ ሥራ ጸሎት ማድረግ ሲሆን ጌታ ራሱ በወንጌላት ቤቴ ለሕዝብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት ይባለል ነበር ያለው፡፡ ቤቱ የጸሎት ቤት እንጂ የሌላ አይደለም፡፡ የሰራናቸው አዳራሾች የጸሎት ቤት ካልሆኑ ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ለመገመት ያስቸግራል፡፡
ማር11፡15-17 ወደ ኢየሩሳሌምም መጡ። ወደ መቅደስም ገብቶ በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ያወጣ ጀመር፥ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጭዎችንም ወንበሮች ገለበጠ፤ 16 ዕቃም ተሸክሞ ማንም በመቅደስ ሊያልፍ አልፈቀደም። 17 አስተማራቸውም፦ ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን? እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት አላቸው። 18 የካህናት አለቆችም ጻፎችም ሰምተው፥ ሕዝቡ ሁሉ በትምህርቱ ይገረሙ ስለ ነበር ይፈሩት ነበርና እንዴት አድርገው እንዲያጠፉት ፈለጉ፡፡
በሦሥቱም ወንጌላት ጌታ ፈሪሳውያንን ከዚህ አንጻር መገሰጹን ተዘግቦ እናገኛለን፡፡ ለጌታ ኢየሱስ ጸሎት ቀዳሚው አጀንዳ ነበር፡፡ የቤተክርስቲያን የክህነትም ሆነ ሌሎች አገልግሎቶች ያለጸሎት ዳር መድረስ አይችሉም፡፡
በዘመናችን ያለችው ቤተክርስቲያን አጸላይ እንጂ ራሳዋ ጸሎተኛ ሆና አትታይም እና ቆም ብላ ራሰዋንንና አገልግሎትዋን መፈተሽ ይጠበቅባታል፡፡ በዘመኑ ጸሎት የጠቅላላ ማህበረ ምእመናን አግልግሎት መሆኑ ቀርቶ ልዩ የጸጋ ሥጦታ ያላቸው ግለሰቦች አገልግሎት ሆኖ ለጥቂቶች ሰዎች ብቻ ተትቶአል፡፡
የቀረው ሕዝብ ለእነርሱ አስፈላጊውን ሁሉ ክፍያ እየከፈለ አገልግሎቱን ሲያገኝ ይስተዋላል፡፡ መነሻው ዋናው የንባብ ክፍላችን ጥቂቶችን ስለምናጸልይበት አገልግሎት ሳይሆን ሁላችንም የጸሎት አገልጋዮች ስለምንሆንበት ዋናው ሥራችን እና ሃላፊነታችን ነው የሚናገረው፡፡ ጸሎት የሁላችንም የአገልግሎት ጥሪ እና የአምልኮአችን አንዱ ክፍል ነው፡፡
መቼስ ብዙ ገንዘብ ስላለው እና ባለጠጋ ስለሆነ ሌላ ሰው እንዲያመልክለት ሰውን የሚቀጥር ስው አለ ብሎ መገመቱ አሰቸጋሪ ቢሆንም በዘመናችን ጸሎት ልዩ ሥጦታ አላቸው ተብሎ ለሚታመኑ ሰዎች መተው እና ጸሎት ትተን ጸላይ ፍለጋ ማነፍነፋችን የሚያመልኩልንን እንደመቅጠር የሚቆጠር ነው፡፡
ሁላችንም አንዱን ጌታ ለማምለክ ተጠርተናል በእንዱ ጌታ የመስቀል ሥራ ወደ እርሱ ለመቅረብ እድል አግኘተናል፡፡ ሁላችንም በአንዱ ጌታ ሞት እና ትንሳኤ ልጆች ሆነናል፡፡ አንዱ ጌታ ብቻ ስለሁላችንም መካከለኛ ሆኖልናል፡፡ በዚሁ ስለ ጸሎት ትእዛዝ በተሰጠበት በንባብ ክፍላችን እርሱ ብቻ መካከለኛ መሆኑ በግልጽ ተጽፎአል፡፡
(1፡5-6 አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ 6 ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤)
ጌታ ኢየሱስ ስለሰዎች ልጆች ሁሉ መካከለኛ ሆኖ ራሱን ስለሁሉ ቤዛ ያደረገው ለእኛ ለሁላችንም በገዛ ደሙ መግባትን እና ወደ አብ መቅረብን ሊሰጠን ነው፡፡ ጸሎት ደሙ ያስገኘልን ወደ አብ ወደ ልጁም ኢየሱስ ወደ ሰማያዊው ንጉስ መቅረባችንን የምንገልጥበት የእለታዊ ሕይወታችን አንዱ ክፍል ነው፡፡
ዕብ 12፡18-24 በደሙ መቅረባችንን እንዲህ ሲል ያስረዳል
18 ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምፅም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፤ 19 ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ፤ 20 እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት የምትለውን ትእዛዝ ሊታገሡ አልቻሉምና፤ 21 ሙሴም፦ እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበር፤ 22 ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፥ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥ 23 በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኵራት ማኅበር፥ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፥ ፍጹማንም ወደ ሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፥ 24 የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል፡፡
ደግሞም ሁላችንም አንዱን ጌታ አባ አባት ብለን የምንጠራበት የልጅነት መንፈስ ተቀብለናል፡፡ ሮሜ 8 እርሱ አባታችን ነው! ይሰማናል፡፡ ነቢያቶች ቢኖሩ እርሱ ሊያደርግልን ያለውን ይነግሩናል እንጂ ራሳቸው ምንም ሊያደርጉሉን አይችሉም፡፡ ለመካኒትዋ ጌታ ልጅ መስጠት ቢፈልግ እና ለነቢያት ቢገለጥላችው ልጅ የመውለድ የተሰፋን መልእክት መገለጡን ይናግራሉ እንጂ ልጅን አይሰጡም፡፡ የብሉይ ኪዳንዋን ሐናን ማሰቡ በቂ ነው፡፡ ሰለዚህ እንደ እርስዋ አንባቸውን የሚያፈሱ እና ደጅ የሚጠኑቱን ጌታ ያስባል፡፡ ስለዚህ አማኞች በጸሎትልንተጋ ይገባል።
ቅድሚያ ጸሎት ለማን ይሆን ቅድሚያ ማግኘት የሚገባው እግዚአብሔር ቅድሚያ የሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ላይ ስንሰበሰብ የመጀሪያው የጸሎት ትኩረት ለነገሥታት ነው፡፡
እግዚአብሔር በመንግሥት በኩል ምን እንዲያደርግ እንፈልጋለን?
የምንኖርበት ሃገር መንግሥት በሕይወታችን ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል ? መንግሥት በዜጐች ላይ ------ እንደሚችል አሎ የሚባል እይደለም ፡፡ ስለዚህ ጥሩ ሕይወት እንድንመራ ለራሳችን እንኳ ስንል ለመንግሥት መጸለይ ይኖርብናል፡፡
ስለ መግንሥት እንጸልይ ስንል መንግሥት ምን አንዲያሳካ ነው መጸለይ ያለብን?
ከላይ በንባብ ክፍሉ በተመለከተው መሠረት
«በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ በሰላምና ደጸጥታ እንድንኖር ነው» በሌላ አነጋገር መንግሥት ሥራውን በአግባብ መሥራት እንዲችል መጸለይ ይኖርብናል ማለት ነው በአንድ ሃገር ውስጥ ዜጐች በነጻነት እና በሰላም መኖር የሚችሉት የሃገሪቱ ሕገ መንግሥት ሲከበር ነው ፡፡
መንግሥት ሕጉን የማውጣት ብቻ ሳይሆን የማስከበር ሥራውን በእገባቡ እንዲወጣ የቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ስለ ነገስታት እና ስለመክዋንንቶችም ትጸልያለች፡፡ በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ተሰግስገን ለመንግስት ከምንሰጠው ድጋፍ ይልቅ በጸሎት የምንሰጠው ድጋፍ ከልክ በላይ ለመንግስትም ሆነ ለአገር ይበጃል፡፡ ፖለቲካ ውስጥ ገብቶ አገርንና ወገንን ማገልገል ትለቅ ዋጋ ያለው ሲሆን ያንን ማድረግ የሚችሉት ለዚህ ጉዳይ ጌታ የጠራቸው ሰዎች ናቸው፡፡ የተቀረነው ግን በጸሎት መንግስትንና የመንግስት አአመራር ላይ ያሉትን የመደገፍ ሃላፊነት አለብን፡፡ አንዲት ሀገር መንግስት አልባ ብተሆን በአገር ላይ የሚመጣው ቀውስ እና ኪሳራ ምን አንደሚመስል ከብዙ አገሮች ተሞክሮ መማር ይቻላል፡፡ ነቢዩ ኤልሳዕ እንደምሳሌ ሊጠቀስ ይችላል። ጸሎታችን ክልል እና ድንበር የለውም ( ቤተክርስቲያን ከፖለቲካ እና ማህበራዊ አደረጃጀት ያለፈ ተልዕኮ ያላት ናት፡፡ የቤተክርስቲያነ ጸሎት ለሁሉ ዘር እና ወገን ነው። ሌላምምሳሌ ከብሉይኪዳንጨምሮ ማያትይቻላል
ኤርም 29:
በእርስዋ ሰላም ሰላም ይሆንላችኋልና ወደ እርስዋ ላስማርክኋችሁ ከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ። 8 የእስራኤልም አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦በመካከላችሁ ያሉት ነቢያቶቻችሁና ምዋርተኞቻችሁ አያታልሉአችሁ፥ እናንተም የምታልሙትን ሕልም አትስሙ። 9 በስሜ ሐሰተኛ ትንቢትን ይናገሩላችኋልና፤ እኔም አልላክኋቸውም። 10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ሰባው ዓመት በባቢሎን በተፈጸመ ጊዜ እጐበኛችኋለሁ፥ ወደዚህም ስፍራ እመልሳችሁ ዘንድ መልካሚቱን ቃሌን እፈጽምላችኋለሁ።
ቤተክርስቲያን ይህን ተልዕኮዋን መወጣቷ በእግዚአብሔር ፊት መልካም እና እርሱን ደስ የሚያሰኝ ነው
የተባላው ለምንድነው መልካም መንግሥት መኖሩን እግዚአብሔር ለምን ይፈልጋል?
III. ለመንግስት/ ለአገር ለምን እንጸልያለን
III. ለመንግስት/ ለአገር ለምን እንጸልያለን
እንግዲህ እግዚአብሔርን በመምሰልና በጭምትነት ሁሉ ጸጥና ዝግ ብለን እንድንኖር፥ ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ። 3-4 ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው
➢ ጸጥ እና ዝግ ብለን እንድንኖር ነው።
1ጢሞ 2፣1-4
ከሁሉ በፊት
ለሰዎች ሁሉ
ለእነማን
ቅድሚያ ጸሎት ለማን ይሆን ቅድሚያ ማግኘት የሚገባው እግዚአብሔር ቅድሚያ የሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ አንድ ላይ ስንሰበሰብ የመጀሪያው የጸሎት ትኩረት ለነገሥታት ነው፡፡
እግዚአብሔር በመንግሥት በኩል ምን እንዲያደርግ እንፈልጋለን?
የምንኖርበት ሃገር መንግሥት በሕይወታችን ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል ? መንግሥት በዜጐች ላይ ------ እንደሚችል አሎ የሚባል እይደለም ፡፡ ስለዚህ ጥሩ ሕይወት እንድንመራ ለራሳችን እንኳ ስንል ለመንግሥት መጸለይ ይኖርብናል፡፡
ስለ መግንሥት እንጸልይ ስንል
መንግሥት ምን አንዲያስብ ነው መጸለይ ያለብን?
ከላይ በንባብ ክፍሉ በተመለከተው መሠረት
«በእውነተኛ መንፈሳዊ ሕይወትና በቅድስና ሁሉ በሰላምና ደጸጥታ እንድንኖር ነው» በሌላ አነጋገር መንግሥት ሥራውን በአግባብ መሥራት እንዲችል መጸለይ ይኖርብናል ማለት ነው በአንድ ሃገር ውስጥ ዜጐች በነጻነት እና በሰላም መኖር የሚችሉት የሃገሪቱ ሕገ መንግሥት ሲከበር ነው ፡፡
መንግሥት ሕጉን የማውጣት ብቻ ሳይሆን የማስከበር ሥራውን በእገባቡ እንዲወጣ የቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
➢ ሰዎች ሁሉ መዳናቸውን የሚወደውን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ስለሆነ
ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲ ደርሱ ነው፡፡ ቁ 4 ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ ሰዎች እውነትን/የወንጌልን/ ከላወቁ የግሞ መዳን አይችሉም፡፡
ስለዚህ ለሰው ሁሉ ወንጌል እንዲነገር የእግዚአብሔር በጐ ፈቃድ ነው
ታዲያ መጠየቅ ያለበት ጥያቄ ወንጌል ለሰው ሁሉ መነገር የሚችለው በበጐ መንግሥት ወይስ በክፋ ሰላም እና መረጋጋት መልካም እና ምቹ የግንኙነት ዕድለ ሲኖር ወይስ ሳይኖር ብለን መጠየቅ ነው ፡፡
የመልካም መንግሥት መታጣት መንስኤዎቹ በርካታ ናቸው፡፡ ነገር ግን ቤተ ክርስቲያን በመልካም መንግሥት መታጣት ውስጥ ሥፍራ የላትም ብሎ ማሰቡ ከቃሉ እውነት ጋር የሚጣረስ ይሆናል፡፡ ስለዚህ በንባብ ክፍላችን መሠረት ለመልካም መንግሥት መታጣት መንስኤ ከሚሆኑ ነገሮች አንዱ፡-
የሚገባንን ያህል አለመጸለያችን ነው ማለት ይቻላል፡፡
ክርስቲያኖች መንግሥትን በልዩ ልዩ መልክ የሚታዩትን ያህል ለመንግሥት/መሪዎች/ አይጸልዩም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ለመንግሥት/ ለአገር መጸለይ የብሉይም ሆነ የአዲስ ኪዳን ግልጽ መርህ ነው፡፡ ለምሳሌ በኤር. 29 ላይ ለእሥራኤል ምርኮኞች የነገረው ለማረካቸው መንግሥት እንዲጸልዩ የሚኖሩበትንም አገር መልካምነት እንዲፈልጉ ነበር፡፡ አዲስ ኪዳንም የካህናት መንግሥት እንደመሆናችን ካህናቱ ስለ ሕዝቡ ወደ እግዚአብሔር እንደሚቀርቡ ቤተ ክርስቲያንም ስለ አገር እና መንግሥት ወደ ሕያው እግዚአብሔር በመቅረብ የክህነት አገልግሎቷን ልትፈጽመው ይገባል፡፡
ሌላኛው ምክንያት፡-
ብንጸልይም እንኳን የጸለይነው የእግዚአብሔርን ፈቃድ በማወቅ አልነበረም ማለት ነው፡፡ የጸለይነውን ነገር ማግኘት የምንችለው እንደፈቃዱ በመጸለይ ነውና፡፡ “እንደፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል” ስለሚል፡፡
መልካም መንግሥት እንዲኖር የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡፡ /መሪዎች የተሾሙት ክፉን ለመቅጣት መልካሙን ለማበረታታት ነውና ሮሜ 13፡፡
እንግዲህ ይህን የተገለጠውን የእግዚአብሔርን ፈቃድ በምድር ላይ ለማስፈጸም ቤተ ክርስቲያን ምንም እንደማይመለከታት ሆና ራስዋን ከሁሉ አግልላ መቀመጥዋ እንዴት አግባብ ይሆናል?
ለቤተ ክርስቲያን ብቻ የተሰጠውንስ የምልጃ ሥራ ከእርሷ ውጪ ማን መከወን ይችላል?
ያለንበት ማሕበረሰብ የሞራል ዝቅጠት በከፋ ደረጃ ላይ መሆኑን እየታዘብን የሥነ ምግባር ልቅነት ቅጥአንባሩን አጥቶ እያየንና እየተገረምን በማማረር እና በመራገም ብቻ መፍትሔ ማምጣት እንዴት እንችላለን?
ቤተ ክርስቲያን ጸሎት አልባ (ሸክም አልባ) ሆና መታየቷ ወሰን የሌለውን የጸሎት ኃይል እና ሥራዋን በሚገባ አለመረዳቷን የሚያሳይ ነው፡፡
ቤተ ክርስቲያን በዓለማችን ላይ ተጽእኖ የማምጣት ኃይሏ ወሰን የሌለው ስለመሆኑ ቃሉ ይናገራል፡፡ ታሪክም ይመሰክራል፡፡
ከጌታ ኢየሱስ የተራራ ስብከቶች ማቴ.5፡13-14 ያለውን ማየት ይቻላል፡፡
I. በተራራ ላይ እንዳለ ከተማ/በግልጽ የሚታይ በምንኖርበት ማሕበረሰብ ውስጥ ከሁሉም አቅጣጫ እንታያለን፡፡ ሰዎች ንግግራችንን ብቻ ሳይሆን ኑሮአችንንም ይመለከታሉ፡፡
I. በተራራ ላይ እንዳለ ከተማ/በግልጽ የሚታይ በምንኖርበት ማሕበረሰብ ውስጥ ከሁሉም አቅጣጫ እንታያለን፡፡ ሰዎች ንግግራችንን ብቻ ሳይሆን ኑሮአችንንም ይመለከታሉ፡፡
II. የዓለም ብርሃን ነን፡- የጨለማ ብቸኛ መፍትሔ ብርሃን ነው፡፡ የብርሃንን ቦታ መያዝ የሚችል ሌላ ነገር የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የዓለም ብርሃን ናት፡፡ ተገቢውን ሚናዋን ባትጫወት የዓለማችንን ጨለማ የሚነቀንቅ ሌላ መፍትሔ ከወዴትም አይመጣም፡
II. የዓለም ብርሃን ነን፡- የጨለማ ብቸኛ መፍትሔ ብርሃን ነው፡፡ የብርሃንን ቦታ መያዝ የሚችል ሌላ ነገር የለም፡፡ ቤተ ክርስቲያን የዓለም ብርሃን ናት፡፡ ተገቢውን ሚናዋን ባትጫወት የዓለማችንን ጨለማ የሚነቀንቅ ሌላ መፍትሔ ከወዴትም አይመጣም፡
➢ እግዚአብሔርን በመምሰል መኖር እንድንችል
ወደ እርሱ መቅረብ በሌለበት እርሱን መምሰል አይኖርም፡፡
1ጴጥሮስ 2፡ 4
(4 በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥ 5 እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ፡፡)
IV. እንዴት እንጸልይ
IV. እንዴት እንጸልይ
➢ አለቁጣ እና ክፉ አሳብ
እንግዲህ ወንዶች በስፍራ ሁሉ አለ ቍጣና አለ ክፉ አሳብ
(ከወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር ያለንን ጤናማ ሕብረት በመጠበቅ) እርስ በእርስ ይቅር በመባባል ካልተመላለስን ጸሎታችን እንቅፋት ይገጥመዋል፡፡ ( ሳል ይዞ ሥርቆት ቂም ይዞ ጸሎት አይሰምርም ይባል የለ)
ማቴ 6፡ 12 እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን
➢ የተቀደሱ እጆችን በማንሳት ( በቅድስና እየተመላለስን)
የተቀደሱትን እጆች እያነሱ እንዲጸልዩ እፈቅዳለሁ::
ወደ ጌታ በደሙ መቅረባችን እርሱን መስለን የምንኖር ልጆቹ ሊያደርገን እንጂ ከእርሱ የምንፈልገውን ብቻ እያገኘን እንደፈለግን ነዋሪዎች ሊያደርገን አይገባም፡፡ ጸሎታችን እና ሕየወታችን የተፋታ ሊሆን አይገባም፡፡ የምንፈልገውንና የምንወደውን የሚሰጠን ጌታ የሚፈልገውን እና እርሱን የሚያስደስተውን ሕይወት እንድንኖር ከእኛ ይፈልጋል፡፡
➢ ሜዳዊነትንና አለማዊነትን በመጸየፍ
እንዲሁም ደግሞ ሴቶች በሚገባ ልብስ ከእፍረትና ራሳቸውን ከመግዛት ጋር ሰውነታቸውን ይሸልሙ፤ እግዚአብሔርን እንፈራለን ለሚሉት ሴቶች እንደሚገባ፥ መልካም በማድረግ እንጂ በሽሩባና በወርቅ ወይም በዕንቍ ወይም ዋጋው እጅግ በከበረ ልብስ አይሸለሙ፡፡ ከሚገባ በላይ በራሱ እና በሌሎች ጉዳዮች የተያዘ ሰው በጸሎት መያዝ አይችልም ( ምን እመስላለሁ ምን እለብሳለሁ ምን እበላለሁ የሚታዩ ፊልሞች ፌስ ቡክ ወሲብ ቀስቃሸ ፊልሞች ወዘተ) ከሚገባ በላይ የምንወሰድባቸው ነገሮች እኛን ጸሎት አልባ የማድረግ ሃይል አላቸው