በደልን ይቅር ማለት (15)

ጸሎትና ይቅርታ  •  Sermon  •  Submitted
0 ratings
· 229 views
Notes
Transcript
Sermon Tone Analysis
A
D
F
J
S
Emotion
A
C
T
Language
O
C
E
A
E
Social
View more →

ወቃሽና ተወቃሽ

ወቃሽ ማን ነው?
ወንድምን ወንድም ብሎ የሚጠጋ ነው። ወቃሽ ማን ነው? ለብቻው ሄዶ ወንድምን የሚወቅስ ነው። ወቃሽ የሚወቅሰው ለምንድር ነው? ወንድምን ገንዘብ ለማድረግ ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለ ምክር ለምን ይመክራል? በደል ወንድምን ያሳጣል። በደል ያመጣው ጉዳት ተበዳይ መበደሉ ሳይሆን በዳይ በመበደሉ ሕይወቱን ወንድምነቱን ማጣቱ ነው።
የመወቃቀስ ትልቁ ተልእኮው

23 ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል አላቸው።

15 ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤

16 ባይሰማህ ግን፥ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፥ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤

17 እነርሱንም ባይሰማ፥ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፥ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።

18 እውነት እላችኋለሁ፥ በምድር የምታስሩት ሁሉ በሰማይ የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈቱት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሆናል።

Num. 35:30; Deut. 17:6; 19:15; John 8:17

አንድ ሰው እርቅን አልሰማም አለ ተብሎ ችግሩን ወደ ቤተ ክርስቲያን ማቅረብ የሚቻለው በዳዩን ወንድም ለማድረግ የሚያስችለውን ሶስት ነገሮች ካደረግን ብቻ ነው። እነዚህ ሶስት መንገዶች የአንድን አገልጋይ ስራ የሚያሳዩ ሳይሆኑ የክርስቲያኖችን ተሳትፎ የሚያመለክቱ ናቸው።
1ኛ ወደ በዳዩ የሚሄደው ተበዳዩ ነው። ይህ ማለት ተበዳይ በዳይ የበደለውን በደል የሚያውቅ መሆን ይኖርበታል። ይህንን ማድረግ የሚገባው አገልጋይ አይደለም።
2ኛ ተበዳይ ወደ በዳይ የሚሄደው በዳይን ለማደስና ለመመለስ ነው።
3ኛ በደል ሁሉ አንድ ነው። ትልቅ በደልና ትንሽ በደል የለም።
4ኛ ይህ የሚደረገው የቤተ ክርስቲያንን ስም ለማስጠበቅ ወይንም በውጭ ያሉ ሰዎች እንዳይታዘቡን አይደለም። የዚህ ዋናው ምክንያት በዳይ የሆነውን ሰው ለማደስና ለመመለስ ነው።
ይህ የሚደረገው የቤተ ክርስቲያንን ስም ለማስጠበቅ ወይንም በውጭ ያሉ ሰዎች እንዳይታዘቡን አይደለም። የዚህ ዋናው ምክንያት በዳይ የሆነውን ሰው ለማደስና ለመመለስ ነው።
ይህ ምን ያስተምረናል?
ይቅርታ በግል የሚደረግ እንዳልሆነ እናያለን። ማንም ሰው ራሱን ለብቻው በመማር ነፃ ነኝ ማለት አይችልም። በሌሎች ሰዎች በኩል ይቅርታ ተቀባይ ሆነን መቅረብ አለብን።
እርቅ ሆነ የሚባለው በዳይ ተበዳይን ይቅር ለማለት ፍላጎት ሲኖር ነው። ተበዳይ በደሉን በማግነን በዳይን ለማሳጣት፣ በዳይ የተባለውን ለመኮነን ወይንም ያንን ሰው ለማፍረስ የሚፈለግ ከሆነ በምንም አይነት እርቅ ሊመጣ አይችልም።
እኛ የተማርነው እንዴት ነው?
ጌታ ኢየሱስ የማረን እንዴት ነው?
በደላችንን መንፈስ ቅዱስ የወቀሰን እንዴት ነው?
መድሐኒት ሆኖልህ እያለ እንዴት በእርሱ አላመንክም? እንዴት ከሐጢያት የምትነጻበት ደም እያለልህ ለምን እስከ አሁን አላመንክም። መንፈስ ቅዱስ እንዲህ እንደሚወቅስ ታምናላችሁን?
ጴጥሮስን ጌታ ኢየሱስ አንዴት ማረው? ጴጥሮስ ትወደኛለህን አያለ ነው ጌታ የጠየቀው።
ይቅርታ ተበዳይ ተኮር ሳይሆን በዳይ ተኮር ነው። በዳይ ተኮር የሆነ ይቅርታ ተበዳይን በበደለው በደል እንዳይጠፋ ማድረግ ነው። በዳይ የሚወቀሰው በተበዳይ ነው። ተበዳይ የሚወቀስበት ምክንያት ገንዘብ እንዲሆን ነው።
ተበዳይና በዳይን ለመለየት የሚቻለው አንዴት ነው?
ለእርቅ የሚሰበሰቡ ሰዎች በጌታ ስም የሚሰበሰቡ ናቸው። የሚሰበሰቡት ለሁለት ነገር ነው። እነዚህን ሁለት ነገሮች አማኞች በተሳሳተ መንገድ እንፈታቸዋለን።
ማሰርና መፍታት የሚሉ ሁለት ቃላት በዚህ ስፍራ ውስጥ ተጠቅሰዋል። ምንድር ነው የሚታሰረው ምንድር ነው የሚፈታው?
Related Media
See more
Related Sermons
See more
Earn an accredited degree from Redemption Seminary with Logos.