Untitled Sermon (15)

Sermon  •  Submitted
0 ratings
· 151 views
Notes
Transcript
Sermon Tone Analysis
A
D
F
J
S
Emotion
A
C
T
Language
O
C
E
A
E
Social
View more →

በመጽሀፍ ቅዱስ ሶስቱም አምላክ ተብለው ተጠርተዋል

የሰውን ልጆች ለማዳን አብ የሰራቸው ስራዎች ምንድር ናቸው?

1. አብ አምላክ እንደሆነ የተጠቀሰባቸ ስፍራዎች
a. ዮሐንስ 6:27 “ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር መብል የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ሥሩ፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።“
b. ሮሜ 1:7 “በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁና ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ በሮሜ ላላችሁት ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።”
c. ገላትያ 1:1 “በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት”
d. ማቴዎስ 11:25 “በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ። አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ“
e. ሐዋርያት ሥራ 3:22 “ሙሴም ለአባቶች። ጌታ አምላክ እኔን እንዳስነሣኝ ነቢይን ከወንድሞቻችሁ ያስነሣላችኋል፤ በሚነግራችሁ ሁሉ እርሱን ስሙት።“
f. 1ኛ ቆሮንቶስ 8:6 “ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን።”
2. ወልድ አምላክ ተብሎ የተጠቀሰባቸው ስፍራዎች
a. ዮሐንስ 1:1 “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ።”
b. ዮሐንስ 20:28 “ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።“
c. የሐዋርያት ሥራ 10:36 “የሁሉ ጌታ በሚሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እየሰበከ ይህን ቃል ወደ እስራኤል ልጆች ላከ።“
d. 2ኛ ጴጥሮስ 1:1 “የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ” አምላካችንና መድሐኒታችን ነው።
d. 2ኛ ጴጥሮስ 1:1 “የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያና ሐዋርያ የሆነ ስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር የተካከለ የክብር እምነትን ላገኙ” አምላካችንና መድሐኒታችን ነው። e. 1ኛ ዮሐንስ 5:20 “የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።” 3. በብሉይይ ኪዳን ለይሆዋ
e. 1ኛ ዮሐንስ 5:20 “የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።”
3. በብሉይይ ኪዳን ለይሆዋ የተነገሩ እውነቶች በአዲስ ኪዳን ለጌታ ኢየሱስ የተነገሩ እንደሆኑ መጽሀፍ ቅዱስ ያሳየናል
በብሉይይ ኪዳን ለይሆዋ የተነገሩ እውነቶች በአዲስ ኪዳን ለጌታ ኢየሱስ የተነገሩ እንደሆኑ መጽሀፍ ቅዱስ ያሳየናል
የተነገሩ እውነቶች በአዲስ ኪዳን ለጌታ ኢየሱስ የተነገሩ እንደሆኑ መጽሀፍ ቅዱስ ያሳየናል
a. በመዝሙረ ዳዊት 102:25 “አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው።” በዚህ በመዝሙር 102 ውስጥ ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔርን በእብራይስጥ ስድስት ግዜ ያህዌ ሲለው ሁለት ግዜ ኤል በማለት ይጠራዋል። በዚህ ክፍል ንጉሥ ዳዊት ያህዌ ያለውን የዕብራውያን መጽሀፍ የጻፈው ጸሐፊ በምዕራፍ 1:10 ላይ “ደግሞ። ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው” በማለት የብሉይ ኪዳኑ ያሕዌህ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ያሳየናል።
b. በኢሳይያስ 45:23 ላይም “ቃሌ ከአፌ በጽድቅ ወጥታለች፥ አትመለስም። ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፥ ምላስም ሁሉ በእኔ ይምላል ብዬ በራሴ ምያለሁ።” ይላል። ይህንን የኢሳይያስን ትንቢት በሙሉ ማንበብ እጅግ ጠቃሚ ነው። በዚህ ክፍል ለእኔ ይንበረከካሉ በማለት ለያህዌህ የተነገረውን በመጥቀስ ሐዋርያት ያንኑ ቃል ለኢየሱስ ክርስቶስ ሲያውሉት ይታያል።
በፊልጵስዩስ 2:10–11 ላይ “ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ 11 መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።” በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም መንበርከካቸው ደግሞም ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ መላስ ሁሉ መመስከሩ ኢየሱስ ከአባቱ ጋር በማይክፈል መለኮታዊ ባሕርይ አንድ ከመሆኑ የተነሳ እንዲህ እንደተባለ ማስተዋል ይኖርብናል።
c. በኢሳይያስ 44:6 ላይ “የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።” በሚለው ቃል ውስጥ እግዚአብሔር የሚለው ቃል በእብራይስጥ ይሆዋ የሚለው መጠሪያ የዋለ ሲሆን ይህንኑ መጠሪያ ናትናኤል የተባለው የጌታ ደቀ መዝሙር በዮሐንስ 1:49 ላይ ጌታ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለው።” በማለት ጌታ ኢየሱስን የእስራኤል ንጉሥ በማለት ሲጠራው እናያለን። ኢሳይያስ የሚቤዠው የእስራኤል ንጉስ ያለው ጌታ ኢየሱስ በእውነትም እስራኤልን የሚቤዥና በእስራኤልም የሚነግሠው ንጉሥ እርሱ ነው። ክብር ለስሙ ይሁን። ኢሳይያስ ከላይ ይሆዋ “እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ” አለ ያለውን የራዕይ መጽሀፍ ጸሐፊውም በምዕራፍ 22:12-13 ላይ ጌታ ኢየሱስ ያንኑ ሲል ይታያል እንዲህ ሲል፦ “እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። 13 አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።“
d. በኢዩኤል 2:32 ላይ “እንዲህም ይሆናል፤ የእግዚአብሔር ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ፥ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም መድኃኒት ይገኛል። ደግሞም እግዚአብሔር የጠራቸው፥ የምስራች የሚሰበከላቸው ይገኛሉ።” ኢዩኤል እግዝዚአብሔር እንዳለው ሆኖ በአማርኛ የተተረጎመው ስም በእብራይስጥኛው መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ ይሆዋ ሆኖ የተጻፈ ነው። ይኸው ቃል በአዲስ ኪዳን በሮሜ 10:13 ላይ “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።” በማለት ስለ ተጠቀሰ ጠርተነው የምንድንበት ስም በአዲስ ኪዳን ከሰማይ በታች ሌላ ስም የለም ስለሚል ኢየሱስ ክርስቶስ የደሕንነት ስም ነው። የሚጣፍጥ ስም። የሚወደድ ስም። በብሉይ ኪዳን እስራኤልን ከግብጽ ሊያድናቸውና ሊታደጋቸው እግዚአብሔር በወረደ ግዜ ራሱን ለሙሴና ለእስራኤል ሕዝብ የገለጠው ይሆዋ በሚለው ስም ነበር። አሁን ደግሞ ከሙሴ የበለጠውን ትልቁን መውጣት ከዓለም፣ ከሰይጣን፣ ከኩነኔና ከዘላለም ሞት አዳኝ ሆኖ የተገለጠው ስሙ ሲጠራ የሚያድነው ኢየሱስ የተባለው ጌታችን እርሱ ኢዩኤል በትንቢቱ የተናገረለት በአዲስ ኪዳን በሥጋ የተገለጠው ጌታ ነው።
e. በዘካርያስ ትንቢት ውስጥ በምእራፍ 12 ውስጥ ከቁጥር 1-10 እንዲህ ይላል፦ “1 ስለ እስራኤል የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፥ ምድርንም የመሠረተ፥ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ 2 እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ለአሕዛብ ሁሉ የመንገድገድ ዋንጫ አደርጋታለሁ፤ ደግሞም ኢየሩሳሌም ስትከበብ በይሁዳ ላይ እንዲሁ ይሆናል። 3 በዚያም ቀን ኢየሩሳሌምን ለአሕዛብ ሁሉ ከባድ ድንጋይ አደርጋታለሁ፤ የሚሸከሙአት ሁሉ እጅግ ይቈስላሉ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በላይዋ ላይ ይከማቻሉ። 4 በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፈረስን ሁሉ በድንጋጤ፥ ተቀማጭንም በእብድነት እመታለሁ፤ ዓይኖቼንም በይሁዳ ላይ እከፍታለሁ፥ የአሕዛብንም ፈረሶች ሁሉ በዕውርነት እመታለሁ። 5 የይሁዳም አለቆች በልባቸው፦ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ብርታት አለ ይላሉ። 6 በዚያ ቀን የይሁዳን አለቆች በእንጨት መካከል እንዳለ ትንታግ፥ በነዶችም መካከል እንዳለ እንደ ፋና ነበልባል አደርጋቸዋለሁ፤ በቀኝና በግራ በዙሪያ ያሉትን አሕዛብ ሁሉ ይበላሉ፤ ከዚያም ወዲያ ኢየሩሳሌም በስፍራዋ በኢየሩሳሌም ትኖራለች። 7 እግዚአብሔርም የዳዊት ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ሰዎች ክብር በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች አስቀድሞ ያድናል። 8 በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋል፤ በዚያም ቀን ከእነርሱ መካከል ደካማው እንደ ዳዊት ይሆናል፤ የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል። 9 በዚያም ቀን በኢየሩሳሌም ላይ የሚመጡትን አሕዛብ ሁሉ ለማጥፋት እጋደላለሁ። 10 በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።” ውድ አድማጮ በዚህ ክፍል ተናጋሪው ማን ነው? ነቢዩ በውስጡ የሚናገረውን እግዚአብሔርን እንዲህ ይላል እያለ እንደሚናገር የሚክድ አለን? ከቁጥር አንድ ጀምሮ እስከ ቁጥር ስምንት ድረስ እግዚአብሔር የሚለው ቃል ሰባት ግዜ ሲጠቀስ በዕብራይስጥኛ ይህ ቃል ይሆዋ ተብሎ የሚነበበውን አራቱን የእብራይስጥኛ ቃላት “ዋይህ ኤችና ውድብልዩ ኤች” ተብለው የተጻፉትን ፊደላት እናያለን። ዘካርያስ እነዚህ ቃላት በትንቢቱ ውስጥ ያስቀመጣቸው እንዲህ እያለ ነበር፦
i. በቁጥር 1 “ስለ እስራኤል የተነገረ የእግዚአብሔር ቃል ሸክም ይህ ነው።”
ii. በቁጥር 1 “የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል”
iii. በቁጥር 4 “በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፈረስን ሁሉ በድንጋጤ፥ ተቀማጭንም በእብድነት እመታለሁ”
iv. በቁጥር 5 “በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ በአምላካቸው በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ብርታት አለ ይላሉ።”
v. በቁጥር 7 “እግዚአብሔርም የዳዊት ቤት ክብርና የኢየሩሳሌም ሰዎች ክብር በይሁዳ ክብር ላይ እንዳይታበይ የይሁዳን ድንኳኖች አስቀድሞ ያድናል።”
vi. በቁጥር 8 “በዚያ ቀን እግዚአብሔር በኢየሩሳሌም ለሚኖሩት ይመክትላቸዋልvii. በቁጥር 8 “የዳዊትም ቤት በፊታቸው እንደ እግዚአብሔር መልአክ እንደ አምላክ ይሆናል።”
ዘካርያስ በዚህ ትንቢት ምን እንደሚያሳየን ልብ እንበል። የሚናገረው ቃል የይሆዋ ቃል እንደሆነ ያሳየናል። የህንን ይሆዋ ደግሞ ሰማይን የዘረጋና ምድርን የመሰረተ ደግሞም የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሰራ እንደሆነ ይናገራል። በዘካርያስ ውስጥ ሆኖ የሚናገረው ይህ ይሆዋ ዋና ተናጋሪ ሆኖ በመጨረሻው ዘመን በአርማጌዶን ጦርነት ግዜ ምን እንደሚያደርግ ያሳየናል “በዚያ ቀን፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ፈረስን ሁሉ በድንጋጤ፥ ተቀማጭንም በእብድነት እመታለሁ፤ ዓይኖቼንም በይሁዳ ላይ እከፍታለሁ፥ የአሕዛብንም ፈረሶች ሁሉ በዕውርነት እመታለሁ።” በማለት ይናገራል። ይህንን ሁሉ የሚያደርገው ይኸ ይሆዋ የተባለው ቅዱስ አምላክ በቁጥር አስር ላይ በአማርኛው መጽሀፍ ቅዱስ ውስጥ “ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።” ወደ እርሱም ወደ ወጉትም ያያሉ የሚለው እራሱን የሚያሳይ እንደሆነ እብራይስጥኛው በደንብ ያሳያል። አማርኛው “ወደ እርሱም” የሚለውን ዕብራይስጥኛው “ወደ እኔም” የሚል ሆኖ የተጻፈ መሆኑን ማወቅ ይገባናል። ሰባ ሊቃናት በመባል የሚታወቀው በግሪክኛ የተተረጎመው የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ ቅዱስ ወደ እኔም የሚል ሆኖ ነው የተጻፈው። ሰባ ሊቃናት የጌታ ሐዋርያት ሲጠቅሱት የነበረ መጽሀፍ ቅዱስ ቅዱስ እንደነበር መርሳት የለብንም። ሐዋርያት ሲጠቅሱት የነበረው ይህ መጽሀፍ ቅዱስ ብቻ ሳይሆን በርካታ ማኑስክሪፕቶችም ሆኑ የእንግዝሊዝኛ የተጻፉ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት “ወደ እኔም ወደ ወጉኝም” ይመለከታሉ” የሚል ትርጉምን ያሳያሉ። በዚህ በቁጥር 10 ላይ “ወደ እኔም ወደ ወጉኝም” ባዩ በዚሁ በዘካርያስ ከምዕራፍ 12 ብቻ ሳንወጣ ራሱን ይሆዋ እያለ የሚጠራው ጌታ አምላክ እንደሆነ ይታያል። በአርማጌዶን ጦርነት ግዜ አይሁድንና ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት የምድር አሕዛብ ሁሉ በሚሰበሰቡበት ግዜ ኢየሩሳሌምና አይሁድን ለመታደር ዳግመኛ እንደሚመጣ ሲነገርለት የኖረው ጌታ ኢየሱስ በሚገለጥበት ግዜ አይሁዳውያን ሁሉ እያዩት ያለቅሳሉ፥ “በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፤ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፤ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኀዘን ያዝኑለታል።” ይህንን የተባረከ መሲህ ክደውት መኖራቸው እንዲሰቀል አላፈው መስጠታቸው እየቆጫቸው ያዝኑለታል። በዚህ ጸጸትና የንስሐ መንፈስ አይሁዳውያን ለአባቶቻቸው ተስፋ ወደ ተገባላቸው የዘላለም በረከት ኢየሱስ ክርስቶስ ያገባቸዋል። ይሆዋ ሆኖ ገልጦ ከሰራላቸው የደሕንነት ስራ የበለጠውን አማኑኤል ሆኖ ጸጋና እውነት የተሞላው የእግዚአብሔር ልጅ፥ አንድያ ልጅ በቸኛው ልጅ፣ በባሕርየ መለኮት ከአባቱ ጋር በሁሉም የተካከለው ጌታ ኢየሱስ በአባቱ ዘንድ ባለው ክብር የከበረው ጌታ የሚመለስበት ቀን ደርሷል። በመከካከለኛው ምስራቅ የሚሆነውን ጆሮ ያለው ይስማ። ኢየሩሳሌም በአሕዛብ ልትከበበብ ቀኑ እየተፋጠነ ነው። ሁኔታው የተመቻቸው ነው። ለእርሱ የማይገዙትን ሊዋጋ የሚመጣው ጌታ አይሁዳውያንን ሊታደግ ይመለሳል። ለዚህ ቀን ራስህን አዘጋጅተሃል? ራስሽን አዘጋጅተሻል?
ዘካርያስ ወደ እርሱም ወደ ወጉትም ያያሉ በማለት በ500 ዓ.ዓ የተናገረውን በራዕይ 1:7 ላይ “እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።” ይላል። ይህ ቀን ለማያምኑ የጭንቅ ቀን ነው። ለአይሁዳውያን መሲሁን አይተው በታላቅ ጸጸትና ንስሐ የሚድኑበት የመታደስ ቀን ነው። ክብርና ምስጋና ቶሎ እመጣለሁ ላለው ደግሞም በደጅ ሆኖ ለቀረበው ጌታ ይሁን። ውድ አድማጮቼ ይህ ጌታ ሊመጣ ባለበት በዚህ ዘመን ኢየሱስን ፍጥሩ አድርጎ ማመን ታላቅ እርግማንና ኩነኔ ነው። ደግሞም በ1ኛ ተሰሎንቄ 1:9-10 ላይ “እነርሱ ራሳቸው ወደ እናንተ መግባታችን እንዴት እንደነበረ ስለ እኛ ይናገራሉና፤ ለሕያውና ለእውነተኛ አምላክም ታገለግሉ ዘንድ፥ ከሙታንም ያስነሳውን ልጁን እርሱንም ኢየሱስን ከሚመጣው ቍጣ የሚያድነንን ከሰማይ ትጠብቁ ዘንድ፥ ከጣዖቶች ወደ እግዚአብሔር እንዴት ዘወር እንዳላችሁ ይናገራሉ።” የሚለውን ማስተዋል ይኖርብናል። ከሚመጣው ቁጣ የሚያድንህ ማን ነው? የሚያድንሽ ማን ነው? ከሚመጣው ቁጣ የሚያድነን ብቸኛው የዓለም መድሐኒት፥ ከሐጢያትና ከጨለማ ስልጣን አዳኝ ኢየሱስ ብቻ ነው። በሐዋርያት ስራ 4:12 ላይ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።” ይህ ቃል የሚናገረው መዳን በሌላ በማንም እንደሌለ ነው። ክሰማይ በታች መዳን የሚቻለው በኢየሱስ ስም ብቻ ነው። ከዚህ ስም ውጪ በማንም መዳን አይቻልም። ኢየሱስን መልዕክተኛ አድርገን እንደ ነቢያትና እንደ መላዕክት ቆጥረን የአምላክ ተላላኪ አድርገን አንድንም። ኢየሱስ ራሱ መድሐኒት ነው። ኢየሱስ ራሱ ሕይወት ነው። ስሙ መድሐኒት የሆነ ከኢየሱስ ማንም ምንም የለም። እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር የፈቀደው የዋጃቸውን እንደ አንዲት ቅንግድ አጭቶ የራሱ እንዲያደርጋቸው የተፈቀደለት ደግሞም በሰማይና በምድር ያለውን ሁሉ የሚጠቀልለው ሁሉ ለእርሱና በእርሱ የሆነ ጌታ ኢየሱስ ብቻ አዳኝ ነው። የሰውን ልጆች ለማዳን አብ የሰራቸው ስራዎች ምንድር ናቸው?

የሰውን ልጆች ለማዳን አብ የሰራቸው ስራዎች ምንድር ናቸው?

በደህንነት ሥራ አብ የሰራቸውና የሚሰራቸው ስራዎች
1. ዓለሙን እንዲሁ የወደደው እርሱ ነው።
2. ዓለሙን እንዲያድን አንድያ ልጁን ሰጠ።
3. ልጁን ወደዚህ ዓለም ሲልክ ለልጁ ክድንግል ማርያም ሰው ሆኖ እንዲወደለድ ሥጋ ያዘጋጀለት እግዚአብሔር አብ ነው።
4. ልጁ ሥጋ ለብሶ ከተገለጠ በኋላ በልጁ ሆኖ የሰውን ልጆች ከራሱ ጋር ለማስታረቅ በልጁ ሆኖ የማስታረቅ ስራ ይሰራ የነበረው እርሱ ነው።
5. ልጁን ከሞት ያስነሳው እግዚአብሔር አብ ነው።
6. ልጁን በቀኙ ያስቀመጠው እግዚአብሔር አብ ነው
7. በአባቱ ቀኝ ከፍ ከፍ ባለው ልጁ ተለምኖ መንፈስ ቅዱስን በአማኞች ላይ እንዲያፈሰው ለልጁ የሰጠው እርሱ ነው
8. ዓለሙን በልጁ ሆኖ ያስታረቀው እርሱ ነው።
9. በሐዋርያት ሆኖ የማስታረቅ ቃል እያኖረ ከእግዚአብሔር የማስታረቁን ሥራ የሠራው እርሱ ነው።
10. የመከሩ ጌታ እርሱ በመሆኑ ወደ መከሩ ሰራተኞችን የሚልከው እርሱ ነው። ስ ለመከሩም የሚለንነው እርሱ ነው።
11. አማኞችን ወደ ልጁ የሚስበውና የሚያስጠጋው እርሱ ነው።
12. ልጁ ከሞት ከተነሳ በኋላ ለቤተ ክርሲቲያን የሰጠው እግዚአብሔር አብ ነው።

በደሕንነት ስራ ወልድ የሰራቸውና የሚሰራቸው ስራዎች

1. የአባቱን ፈቃድ ለማድረግ ወደ ምድር ተልኮ የመጣው ወልድ ነው
2. በምድር ሳለ አባቱ ሲያደርግ ያየውን የሰማውን እያስተዋለ በእርሱ ሆኖ የሚሰራውን አብን እያከበረ ያገለገለው ወልድ ነው።
3. በምድር ላይ የተመላለሰው የራሱን ፈቃድ በማድረግ ሳይሆን የአባቱን ፈቃድ ብቻ በማድረግ ነው።
4. ለመስቀል ሞት የታዘዘው የአባቱን ፈቃድ ለመፈጸም ነው።
5. ነፍሱን ለበጎቹ አሳልፎ ሰጠ።
6. በሰማይ በአባቱ ቀኝ የዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።
7. በደሙ የተዋጁትን የራሱ ቤተ ክርስቲያን አድርጎ የሚሰራቸው እርሱ ነው።
8. እርሱ የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው። 9. ቤተ ክርስቲያን አካሉ ናት።
በደሕንነት ሥራ መንፈስ ቅዱስ የሰራቸውና የሚሰራቸው ስራዎች
1. ጌታችን ከድንግል ሊወለድ የቻለው በመንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ነው።
2. ጌታችን ያደገው በመንፈስ ቅዱስ ሐይልና ጸጋ ነው።
3. ጌታችን ወንጌልን እንዲሰብክ በላዩ ሆኖ ሐይልና ጸጋ የሰጠው መንፈስ ቅዱስ ነው።
4. ጌታችን አጋንንትን ሲያወጣ በመንፈስ ቅዱስ ጣትና ሐይል ነው።
5. ጌታችን ከዲያብሎስ ሊፈተን ወደ ምድረ በዳ የተወሰደው በመንፈስ ቅዱስ ነበር።
6. ጌታችን በመሥቀል ላይ ያፈሰሰውን ደሙን ለእግዚአብሔር ያቀረበው በዘላለም መንፈስ ነው።
7. መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሚወጣ መንፈስ ነው።
8. መንፈስ ቅዱስ የሌለው የክርስቶስ ወገን አይደለም።
9. በመንፈስ ቅዱስ ካልሆነ በቀር ማንም ክርስቶስ ጌታ ነው ሊል አይችልም።
10. የክርስቶስ ኢየሱስ አካል የምንሆነው መንፈሱን ከጠጣንና በመንፈሱ ከተጠመቅን ነው።
ካርል ባርት የተባለው ሰው የክርስቶስ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ በክርስቲያኖች ሕይወት ተግባራዊ እንዲሆን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ አለባቸው አለ። የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት አማኞች የእግዚአብሔር ልጆች መሆናቸውን እንዲያውቁና እንዲያስተውሉ የሚያደርግ መንፈሳዊ ንቃት የሚያስገኝ እንደሚሆን የሚያምን ሰው ነበር። የባርት የስነ መለኮት ቅኝት በክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ ማዕክልነት ላይ የተማከለ ነው። መንፈስ ቅዱስ በክርስቶስ የመጣውን መገለጥ የሚያስገነዝብና በጥልቀት እንድንረዳ የሚያደርግ እንጂ አዲስ መገለጥ የሚያመጣ አይደለም። ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ የሚለው የሐዋርያው ዮሐንስ ትምሕርት የእውነትና የስሕተት ነገር መለያው ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ ነው የሚያስተምረን።
Related Media
See more
Related Sermons
See more