በክርስቶስ ማንነት ማወቅ (17)
ኢየሱስ ክርስቶስ • Sermon • Submitted
0 ratings
· 824 viewsበክርስቶስ ኢየሱስ የሚኖረውን አዲስ ሕይወት ለመኖር ፍቅሩ ግድ ሊለን ይገባል፡፡
Notes
Transcript
Sermon Tone Analysis
A
D
F
J
S
Emotion
A
C
T
Language
O
C
E
A
E
Social
በክርስቶስ ማንነት ማወቅ
በክርስቶስ ማንነት ማወቅ
2 Cor
ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ። ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም። ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል። ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ። እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን። እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።
የኢየሱስ ፍቅር ግድ ይለናል ማለት ምን ማለት ነው? ቃሉ በግሪክ συνέχει ሱኔኬይ ማለት ሲሆን የሚያሳየው ትርጉም መማረክን፣ ግድ ማለትን፣ ሃሳብን ሁሉ መያዝንና ማስገድድን የሚያሳይ ቃል ነው፡፡ ሰው በብዙ መንገድ ተገዶ እንዲኖር ይሆናል፡፡ በባለ ስልጣን፣ በሐይል፣ በፍርሃትና በይሉኝታ ከልቡ ያልሆነውን ነገር ለማድረግ ይገደዳል፡፡ ጳውሎስ እኛን ግድ የሚለን፣ ሃሳባችንን የሚይዘውና የሚማርከን የክርስቶስ ፍቅር ነው ይላል፡፡ በክርስቶስ ፍቅር ተገደው እንዲኖሩ የሆኑት ከምን የተነሳ ነው? ምክንያቶቹን ጳውሎስ ያሳይል፡፡
የክርስቶስ ፍቅር ግድ የሚለን አንዱ ጌታ ለሁሉ በመሞቱ ነው፡፡ የእርሱ ሞት የሞተላቸው ሰዎች ሁሉ ሞት ስለሆነ ሁሉም ስለ ሞቱ ፍቅሩ ግድ ይለናል፡፡
ለሁሉም ስለ ሞተ በሕይወት ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሳው እንጂ ለራሳቸው እንዳይኖሩ የሞተ ስለ ሆነ ፍቅሩ ግድ ይለናል፡፡
ይህ የጌታ ሞት ካመጣው ለውጥ የተነሳ ስለ ራሳችንም ሆነ ስለሌላ ሰው ያለንን አመለካከት ለውጦታል ይላል፡፡
የጌታ ኢየሱስ ሞት እኛን ለእኛ ከመኖር ያዳነ ብቻ ሳይሆን የእኛንም ማንነት የለወጠ ነው፡፡ የምንታወቀው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ምክንያቱም
