Untitled Sermon

Sermon  •  Submitted
0 ratings
· 16 views
Notes
Transcript
1 Kings 18:46 AMTAB
የእግዚአብሔርም ኀይል በኤልያስ ላይ ወረደ፤ ኤልያስም ልብሱን ከፍ አድርጎ በቀበቶው ካጠበቀ በኋላ እስከ ኢይዝራኤል ድረስ አክዓብን ቀድሞት ሮጠ።
2 Samuel 20:8 AMTAB
በገባዖን ከታላቁ ቋጥኝ አጠገብ ሳሉ፣ አሜሳይ ሊገናኛቸው መጣ፤ ኢዮአብ የጦር ሜዳ ልብሱን ለብሶ ሰይፉን ከሰገባው በወገቡ ላይ ታጥቆ ነበር፤ ወደ ፊት ራመድ እንዳለም ሰይፉ ከሰገባው ወጥቶ ወደቀ።
1 Kings 2:5 AMTAB
የጽሩያ ልጅ ኢዮአብ በእኔ ላይ ያደረገውን፣ እንዲሁም በእስራኤል ሰራዊት አዛዦች በኔር ልጅ በአበኔርና በዬቴሩ ልጅ በአሜሳይ ላይ የፈጸመውን አንተው ራስህ ታውቃለህ፤ ጦርነት ሳይኖር በሰላሙ ጊዜ ደማቸውን አፍሶአል፤ በዚህም ደም ወገቡ ላይ የታጠቀውን ቀበቶና በእግሩ ላይ ያደረገውን ጫማ በክሎአል።
2 Kings 4:29 AMTAB
ኤልሳዕም ግያዝን፣ "እንግዲህ ወገብህን ታጠቅ፤ በትሬን ያዝና ሩጥ፤ መንገድ ላይ ሰው ብታገኝ ሰላም አትበል፤ ማንም ሰው ሰላም ቢልህ መልስ አትስጥ፤ በትሬንም በልጁ ፊት ላይ አድርግ" አለው።
2 Kings 9:1 AMTAB
ነቢዩ ኤልሳዕ ከነቢያት ማኅበር አንዱን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ "ወገብህን ታጥቀህ፣ ይህን የዘይት ማሰሮ በመያዝ በሬማት ወደምትገኘው ገለዓድ ሂድ።
Psalm 109:19 AMTAB
ገላውን እንደሚሸፍንበት ልብስ፣ዘወትር እንደሚታጠቀውም መቀነት ትሁነው።
Isaiah 5:27 AMTAB
በመካከላቸው ደካማና ስንኩል አይገኝም፤የሚያንቀላፋና የሚተኛ አይኖርም፤የወገባቸው መቀነት አይላላም፤የጫማቸውም ማሰሪያ አይበጠስም።
Jeremiah 13:1–11 AMTAB
እግዚአብሔር፣ "ሄደህ ከተልባ እግር የተሠራ መቀነት ግዛ፤ ወገብህንም ታጠቅበት፤ ነገር ግን ውሃ አታስነካው" አለኝ። ስለዚህ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ መቀነቱን ገዛሁ፤ ወገቤንም ታጠቅሁበት። ለሁለተኛም ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤ "ገዝተህ የታጠቅህበትን መቀነት ይዘህ፣ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፤ በዚያም በዐለት ንቃቃት ውስጥ ሸሽገው።" ስለዚህ እግዚአብሔር በነገረኝ መሠረት ወደ ኤፍራጥስዠ ሄጄ ሸሸግሁት። ከብዙ ቀን በኋላም እግዚአብሔር፣ "ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፤ በዚያ እንድት ሸሽገው የነገርሁህን መቀነት አምጣ" አለኝ። እኔም ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ፤ መታጠቂያውን ከሸሸግሁበት ቦታ ቈፍሬ አወጣሁ፤ መታጠቂያውም ተበላሽቶ፣ ከጥቅም ውጭም ሆኖ ነበር።የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፤ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ 'የይሁዳን ትዕቢትና የኢየሩሳሌምን እብሪት እንደዚሁ አጠፋለሁ። ቃሌን መስማት እምቢ ብለው በልባቸው እልኸኝነት በመሄድ ሊያመልኳቸውና ሊሰግዱላቸው ሌሎችን ጣዖቶች የሚከተሉ እነዚህ ክፉ ሕዝቦች ከጥቅም ውጭ እንደሆነው እንደዚህ መቀነት ይበላሻሉ። መቀነት በሰው ወገብ ላይ እንደሚታሰር፣ መላው የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ከእኔ ጋር ተጣብቆ ለስሜ ምስጋናና ክብር፣ የኔ ሕዝብ እንዲሆንልኝ አድርጌው ነበር፤ ሕዝቤ ግን አልሰማም' ይላል እግዚአብሔር።
Daniel 10:5 AMTAB
ቀና ብዬ ስመለከት፣ በፊቴ በፍታ የለበሰና በወገቡም ላይ ምርጥ የወርቅ ቀበቶ የታጠቀ አንድ ሰው አየሁ።
Matthew 10:9 AMTAB
በመቀነታችሁ ወርቅም ሆነ ብር ወይም መዳብ አትያዙ።
Mark 6:8 AMTAB
ይህንንም ትእዛዝ ሰጣቸው፤ "ለመንገዳችሁ ከበትር በስተቀር፣ እንጀራ ወይም ከረጢት ወይም ደግሞ ገንዘብ በመቀነታችሁ አትያዙ፤
Acts 21:11 AMTAB
ወደ እኛም መጣና የጳውሎስን መታጠቂያ ወሰደ፤ የራሱንም እጅና እግር በማሰር፣ "መንፈስ ቅዱስ፣ 'በኢየሩሳሌም ያሉ አይሁድ የዚህን መታጠቂያ ባለቤት እንዲህ አድርገው በማሰር ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል' ይላል" አለ።
1 Samuel 18:4 AMTAB
ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከነጦር ልብሱ፣ በተጨማሪም ሰይፉን፣ ቀስቱንና መታጠቂያውን ሰጠው።
2 Samuel 18:11 AMTAB
ኢዮአብም ይህን የነገረውን ሰው፣ "ምን አልህ! ካየኸው ታዲያ ለምንድን ነው ያኔውኑ መተህ መሬት ላይ ያልጣልኸው? ይህን አድርገህ ቢሆን ኖሮ፣ ዐሥር ሰቅል ጥሬ ብርና የጀግና ሰው ቀበቶም እሸልምህ ነበር" አለው።
Ezekiel 23:15 AMTAB
እነርሱም ወገባቸውን በቀበቶ የታጠቁና በራሳቸው ላይ ተንጠልጣይ ያለው ጥምጥም የጠመጠሙ ነበሩ፤ ሁሉም የከለዳውያንተወላጆችና የባቢሎን ሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር።
2 Kings 1:8 AMTAB
እነርሱም "ሰውየው ጠጒራም ልብስ የለበሰ ነው፤ በወገቡም ላይ ጠፍር ታጥቆአል" አሉት።ንጉሡም፣ "ዐወቅሁት፤ ቴስብያዊው ኤልያስ ነው" አላቸው።
Matthew 3:4 AMTAB
የዮሐንስ ልብስ የግመል ጠጕር ሲሆን፣ ወገቡንም በጠፍር ይታጠቅ ነበር። ምግቡም አንበጣና የበረሃ ማር ነበር።
Mark 1:6 AMTAB
ዮሐንስ የግመል ጠጒር ይለብስ፣ በወገቡ ጠፍር ይታጠቅ፣ አንበጣና የበረሓ ማር ይበላ ነበር።
Isaiah 11:5 AMTAB
ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣ታማኝነትም የጐኑ መቀነት ይሆናል።
Ephesians 6:14 AMTAB
እንግዲህ ወገባችሁን በእውነት ዝናር ታጥቃችሁ፣ የጽድቅንም ጥሩር ለብሳችሁ፣
Related Media
See more
Related Sermons
See more