Sermon • Submitted • Presented
0 ratings
· 79 viewsFiles
Notes
Transcript
እግዚአብሔርን መፍራትና መንፈሳዊ
ሕይወት
“17 ልብህ በኃጢአተኞች አይቅና፤ ነገር ግን
ቀኑን ሙሉ እግዚአብሔርን በመፍራት ኑር፤
18 በእውነት ፍጻሜ አለህና፥ ተስፋህም
አይጠፋምና”
ምሳሌ 23፥17-18
እግዚአብሔርን መፍራት ማለት ምን ማለት ነው?
ፍርሃት፣
መጨነቅ፣
መንቀጥቀጥ፣
ረዓድ፣
ማደንገጥ
የያዕቆብ መመኪያ
“የአባቴ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሃት ከእኔ ጋር ባይሆንስ ዛሬ
ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፤ እግዚአብሔር መከራዬንና የእጆቼን ድካም
አየ፥ ትናንትም ገሠጸህ” ዘፍ. 31፥42
“የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ የአባታቸውም አምላክ በእኛ
መካከል ይፍረድ። ያዕቆብም በአባቱ በይስሐቅ ፍርሃት ማለ” ዘፍ.
31፥53
እግዚአብሔርን መፍራት የመሲሁ መሰረታዊ ባሕርይ ነው
ኢሳይያስ 11፥1-5
1፤ ከእሴይ ግንድ በትር ይወጣል፥ ከሥሩም ቍጥቋጥ ያፈራል።
2፤ የእግዚአብሔር መንፈስ፥ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ፥ የምክርና የኃይል
መንፈስ፥ የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
3፤ እግዚአብሔርን በመፍራት ደስታውን ያያል። ዓይኑም እንደምታይ
አይፈርድም፥ ጆሮውም እንደምትሰማ አይበይንም፤
4፤ ነገር ግን ለድሆች በጽድቅ ይፈርዳል፥ ለምድርም የዋሆች በቅንነት
ይበይናል፤ በአፉም በትር ምድርን ይመታል፥ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን
ይገድላል።
የንጉሥ ዳዊት ልመናዎች
መዝሙር 19፥7-11
7 የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር
ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።
8 የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤
የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።
9 የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤
የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው።
10 ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም
ይጣፍጣል።
የንጉሥ ዳዊት ልመናዎች
11 ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።
12 ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።
13 የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ
ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።
14 አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ
ያማረ ይሁን።
ሐዋርያት አገልግሎታቸውን የሚያከናውኑት በእግዚአብሔር ፍርሃት ነው
“11 እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን ሰዎችን እናስረዳለን
ለእግዚአብሔር ግን የተገለጥን ነን፤ በሕሊናችሁም ደግሞ የተገለጥን
እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ። 12 በመልክ እንጂ በልብ ለማይመኩ
የምትመልሱላቸው መልስ እንዲኖራችሁ፥ በእኛ ልትመኩ ምክንያት
እንሰጣችኋለን እንጂ ራሳችንን ደግሞ ለእናንተ የምናመሰግን
አይደለንም”
2ኛ ቆሮ. 5፥11-12
እግዚብሔርን ለማያምኑ የእግዚአብሔር ፍርሃት
ድንጋጤ ነው
“ከእግዚአብሔር ማስደንገጥና ከግርማው ክብር የተነሣ ወደ ድንጋይ
ዋሻ ግባ፥ በመሬትም ውስጥ ተሸሸግ” ኢሳ. 2፥10
“ከእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ድንጋጤ ስለ ወደቀባቸው በጌራራ
ዙሪያ የነበሩትን ከተሞች ሁሉ መቱ፤ በከተሞቹም ውስጥ እጅግ
ብዝበዛ ነበረና ከተሞቹን ሁሉ በዘበዙ” 2ኛ ዜና. 14፥14
እግዚብሔርን የሚያስደነግጣቸው ሳይፈሩት የነበሩትን ሰዎች
ነው
“አብርሃምም አለ፡— በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት
እንደሌለ፥ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው” ዘፍጥረት
20፥11
ኃጢአተኛ በራሱ የሚያስት ነገርን ይናገራል፥ የእግዚአብሔርም ፍርሃት
በዓይኖቹ ፊት የለም” መዝ. 36፥1
እግዚብሔርን የሚያምኑ ኑሮአቸውን የሚመሩት በፍርሃቱ ነው
“ዖፅ በሚባል አገር ስሙ ኢዮብ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፤ ያም ሰው
ፍጹምና ቅን፥ እግዚአብሔርንም የሚፈራ፥ ከክፋትም የራቀ ነበረ” ኢዮ.
1፥1
“አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም
በእግዚአብሔር ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት መማለጃም መውሰድ
የለምና ሁሉን ተጠንቅቃችሁ አድርጉ አላቸው” 2ኛ ዜና 19፥7
“ወንድሜን አናኒንና የግንቡን አለቃ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ
ሾምኋቸው፤ እርሱም እውነተኛ ከሌሎቹም ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ
እግዚብሔርን ለሚፈሩ የሚኖራቸው በረከቶች
“12 እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ
ያስተምረዋል። 13 ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን
ይወርሳል። 14 እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ ቃል
ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል” መዝ. 25፥12-14
“አሁንም እግዚአብሔርን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም
በእግዚአብሔር ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት መማለጃም መውሰድ
የለምና ሁሉን ተጠንቅቃችሁ አድርጉ አላቸው” 2ኛ ዜና 19፥7
“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥
ያድናቸውማል” መዝ. 34፥7
እግዚብሔርን ለሚፈሩ የሚኖራቸው በረከቶች
መዝ. 112
“1 ሃሌ ሉያ። እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ
ሰው ምስጉን ነው።
2 ዘሩ በምድር ላይ ኃያል ይሆናል፤ የቅኖች ትውልድ ትባረካለች።
3 ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘላለም ይኖራል።
4 ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፤ መሓሪና ይቅር ባይ ጻድቅም
ነው።
5 ቸር ሰው ይራራል ያበድራልም፥ በፍርድም ነገሩን ይፈጽማል።
እግዚብሔርን ለሚፈሩ የሚኖራቸው በረከቶች
መዝ. 112
“ 6 ለዘላለም አይናወጥም፤ የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል።
7 ከክፉ ነገር አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው።
8 በጠላቶቹ ላይ እስኪያይ ድረስ ልቡ ጽኑ ነው፥ አይፈራም።
9 በተነ ለችግረኞችም ሰጠ፤ ጽድቁ ለዘላለም ዓለም ይኖራል፤ ቀንዱ
በክብር ከፍ ከፍ ይላል።
10 ኃጢአተኛም አይቶ ይቈጣል፥ ጥርሱንም ያፋጫል፥ ይቀልጣልም፤
የኃጢአተኞችም ምኞት ትጠፋለች።
እግዚብሔርን ለሚፈሩ የሚኖራቸው በረከቶች
መዝ. 128
1 እግዚአብሔርን የሚፈሩት ሁሉ፥ በመንገዶቹም የሚሄዱ ምስጉኖች
ናቸው።
2 የድካምህንም ፍሬ ትመገባለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም
ይሆንልሃል።
3 ሚስትህ በቤትህ እልፍኝ ውስጥ እንደሚያፈራ ወይን ናት፤ ልጆችህ
በማዕድህ ዙሪያ እንደ ወይራ ቡቃያ ናቸው።
4 እነሆ፥ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው እንዲህ ይባረካል።
እግዚብሔርን ለሚፈሩ የሚኖራቸው በረከቶች
“እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤ የሚፈራውም ጠግቦ
ይኖራል፥ ክፉ ነገርም አያገኘውም።” ምሳሌ 19፥23
“ሁልጊዜ የሚፈራ ሰው ምስጉን ነው፤ ልቡን የሚያጸና ግን በክፉ ላይ
ይወድቃል” ምሳሌ 28፥14
” እግዚአብሔርን የሚፈራ ከሁሉ ይወጣልና ይህን ብትይዝ ከዚያም
ደግሞ እጅህን ባታርቅ መልካም ነው” መክብብ 7፥18
“እግዚአብሔርን የሚፈራ ፈቃዱንም የሚያደርግ ቢኖር ያንን እግዚአብሔር
ይሰማዋል እንጂ ኃጢአተኞችን እንዳይሰማ እናውቃለን” ዮሐንስ 9፥31
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው በፊቱ ይኖራል
1፤ ዮሴፍ ግን ወደ ግብፅ ወረደ፤ የፈርዖን ጃንደረባ የዘበኞቹም አለቃ የሚሆን የግብፅ
ሰው ጲጥፋራ ወደ ግብፅ ካወረዱት ከእስማኤላውያን እጅ ገዛው። 2፤ እግዚአብሔር
ከዮሴፍ ጋር ነበረ፥ ሥራውም የተከናወነለት ሰው ሆነ፤ በግብፃዊው ጌታውም ቤት
ነበረ። 3፤ ጌታውም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንዳለ፥ እርሱ የሚሠራውንም ሁሉ
እግዚአብሔር በእጁ እንዲያከናውንለት አየ። 4፤ ዮሴፍም በጌታው ፊት ሞገስን አገኘ፥
እርሱንም ያገለግለው ነበር፤ በቤቱም ላይ ሾመው፥ ያለውንም ሁሉ በእጁ ሰጠው። 5፤
እንዲህም ሆነ፤ በቤቱ ባለውም ሁሉ ላይ ከሾመው በኋላ እግዚአብሔር የግብፃዊውን
ቤት ስለ ዮሴፍ ባረከው፤ የእግዚአብሔር በረከት በውጪም በግቢም ባለው ሁሉ ላይ
ሆነ።
6፤ ያለውንም ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ፤ ከሚበላውም እንጀራ በቀር ምንም
የሚያውቀው አልነበረም። የዮሴፍም ፊቱ መልከ መልካምና ውብ ነበረ። ፤ ከዚህም
በኋላ እንዲህ ሆነ፤ የጌታው ሚስት በዮሴፍ ላይ ዓይንዋን ጣለች። ከእኔም ጋር ተኛ
አለችው። 8፤ እርሱም እንቢ አለ፥ ለጌታውም ሚስት እንዲህ አላት። እነሆ ጌታዬ በቤቱ
ያለውን ምንም ምን የሚያውቀው የለም፥ ያለውንም ሁሉ ለእኔ አስረክቦኛል፤ 9፤ ለዚህ
ቤት ከእኔ የሚበልጥ ሰው የለም፤ ሚስቱ ስለ ሆንሽ ከአንቺም በቀር ያልሰጠኝ ነገር
የለም፤ እንዴት ይህን ትልቅ ክፉ ነገር አደርጋለሁ? በእግዚአብሔር ፊት እንዴት
ኃጢአትን እሠራለሁ?
10፤ ይህንም ነገር በየዕለቱ ለዮሴፍ ትነግረው ነበር፤ እርሱም ከእርስዋ ጋር ይተኛ
ዘንድ ከእርስዋም ጋር ይሆን ዘንድ አልሰማትም።
እግዚአብሔር የሚፈራ ሰው ፍጻሜ አለው