Untitled Sermon (3)
Sermon • Submitted
0 ratings
· 8 viewsNotes
Transcript
Handout
1.1. በስታይልና በስልት(ቲክኒክ)፣ በሕግና በመርህ መካከል ያለው ልዩነት
1.1. በስታይልና በስልት(ቲክኒክ)፣ በሕግና በመርህ መካከል ያለው ልዩነት
§ ስታይል ግላዊ ምርጫ በመሆኑ ከሰባኪ ወደ ሰባኪ ይለያያል፣
§ ስልት ደግሞ ለምንፈልገው ግልጋሎት እንዲውል የሚመች አቀራረብ በመሆኑ ከአድማጭ አድማጭ ይለያያል።
o ለምሳሌ ስብከቱ የሚቀርበው በግብርና ሙያ ለሚተዳደር ማኅበረሰብ ነውን? ወይስ የከፍተኛ ተቋም ትምህርታቸው ላጠናቀቁ? የስብከቱ የአቀራረብ ስልት ከአድማጭ ወደ አድማጭ መለያየቱ የግድ ነው። አሊያ አየር መጎሰም ነው።
§ ደንብ አውዳዊ አገባቡን ጠብቆ የሚለዋወጥ ነገር ባለመሆኑ ግትር ነው። ስለዚህ አውዱ ሲለወጥ፣ ደንብም አብሮ መለወጡ የግድ ነው። መርህ ግን ከሁሉ ነገር ጀርባ ያለ እውነት ስለሆነ አይለወጥም፣ በሁሉም አይነት አገባብ ሥር በሥራ መተርጎም ይችላል።
· ስለዚህ የዚህ ክፍለ ጊዜ አላማ፣ ስለ ቴክኒክ ወይም ስታይል ወይም የስብከት ሕግ ሳይሆን፣ ስለ መርህ መጨበጥ ነው።
1.2. የስብከት ዓላማ
Thomas Goodwin “እግዝብሔር አንድ ልጅ ብቻ ነበረው፣ እርሱንም ሰባኪ አደረገው”” God only had one son, and he made him a preacher.” ማርቆስ ስለ ክርስቶስ አገልግሎት ጅማሬ ሲናገር “ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከ…ወደ ገሊላ መጣ” (Mark 1:14)[1]
· ጳውሎስ ነፍሱን እንድ ቁርባን መጠጥ እየፈሰሰ፣ ኑዛዜው - ቃሉን ስብከ!
· በዘምኑ ሁሉ ለዚህ ወንጌል መከራን ተቀቧል
· ዛሬም የሚያስፈልገን ከስብከት ማፈግፈግ ሳይሆን፣ በጥራት የሚሰብኩ የታጠቀና የሰለጠኑ፣ ሰባኪያንን ማምረት ነው
የስብከት ዓላማ እግዚአብሔር ተኮር ነው
የስብከት ግብ ሰባኪው እንዲሁም አድማጮቹ በአንድነት ሆነው እግዚአብሔርን ያውቁትና ይወዱት ዘንድ፣ እግዚአብሔርንም ከማወቃቸውና ከመውደዳቸው የተነሳ እግዚአብሔር ባስቀመጣቸው ሁኔታ ውስጥ ተገቢ ምላሽ እየሰጡ፣ ክርስቶስን እየመሰሉ፣ ለስሙ ምስክር ሆነው እንዲኖሩ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔርን ማወቅ ለአማኝ ሁሉ የሕይወት ግብ ነው (ኤር 9:23-24; ዮሐ 17:3; ፊል 3:10; ዘዳ 6:5; ማቴ 22:37; ሚል 6:8; ቆላ 3:9-10; ሮሜ 8:29)።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤
“ጥበበኛ በጥበቡ አይታበይ፤
ኀያልም በኀይሉ አይመካ፤
ሀብታምም በሀብቱ አይኵራራ፤
የሚመካ ግን፣
እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ በማወቁና፣
በምድር ላይ ምሕረትን፣ ፍትሕንና ጽድቅን የማደርግ መሆኔን በመረዳቱ፣
በዚህ ይመካ፤ እኔ በእነዚህ ነገሮች፣
እደሰታለሁና፤”
ይላል እግዚአብሔር።
[1] “ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ።”